January 16, 2007

A Tale of Two Synods, Two Patriarchs

የሁለት ሲኖዶሶች እና ፓትርያርኮች ወግ
ነመራ ዋቀዮ ቶላ
በቅርቡ የሰማነውና በትልቅ ተስፋ የጠበቅነው በሁለቱ ፓትርያርኮች መካከል ሊጀመር የነበረው ውይይት ሳይወለድ መክኖ፣ ሳይተኮስ ደንብሾ፣ ሳይጀመር ተፈጽሞ፣ ይመጣል ተብሎ የተጠበቀው አስተዳደራዊ አንድነትም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ያልተገመተ ውጤት ባይሆንም የቤተ ክርስቲያኒቱ መጻዒ ሁኔታ ለሚያሳስባቸው ግን እንዲሆን የተፈለገ መደምደሚያ አልነበረም፡፡ ይሁን እንጂ የተፈራው ደርሷል፡፡ ውይይቱም ሳይካሔድ ቀርቷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ ልዩነት እንዲቀጥል ለሚፈልጉ ወገኖችም ትልቅ እፎይታን ፈጥሯል፡፡
የዚህን ውይይት አለመሳካት በግሌ የምመለከተው በሚከተሉት ሁለት ሁኔታዎች መነጽር ነው፡፡


ሀ. ሁኔታ አንድ
1. ‹‹ነአምን በአሐዱ አምላክ›› የሚሉ አባቶችና ‹ሲኖዶሶች›፣
2. አንዲት ቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉ አባቶችና ‹ሲኖዶሶች› እንዲሁም ፓትርያርኮች፣
3. አንዲት ቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስስቲያንን የሚወክሉ ‹ሦስት› አስተዳደሮች፡፡ እነርሱም የአገር ቤቱ ‹የአባ ጳውሎስ› አስተዳደር፣ የዳያስጶራው የአባ ‹መርቆርዮስ› (የአባ መልከጼዴቅ አስተዳደር እንጂ የቀድሞው ፓትርያርክ አይደለም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ቢበዙም) አስተዳደር፣ እና ‹ገለልተኛው› የሁለቱም አይደለሁም ባዩ አስተዳደር፣ እንዲሁም በሁሉም በኩል ያሉ አያሌ አገልጋዮች ካህናትና ምዕመናን፡፡
ለ. ሁኔታ ሁለት
1. ቅን መሪ እረኛ-አባት ያጡ በጎች-ምእመናን፣
2. ነጻነት የሌላቸውና የተለያዩ ፍላጎቶች ባሏቸው ወገኖች የሚዘወሩ (እነርሱም በአገር ውስጥ ያለው በመንግሥት፣ በዳያስጶራ ያለው አብዛኛው ደግሞ በ‹ተቃዋሚዎች›) ሦስት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደሮች ፡፡
3. የአክራሪ እስላሞች ሰይፍ ‹ከዛሬ ነገ› እያለ ተስሎ የሚጠብቀው ክርስቲያንና ቤተ ክርስቲያን፣
4. የፕሮቴስታንቶች ቅሰጣ ያስበረገገው ምዕመን፣
5. ጠባቂና ረዳት ያጡ ገዳማትና አድባራት፣ አበው ሊቃውንትና ቅርሦች፣
6. ጵጵስናን ብቻ ተስፋ የሚያደርጉ ደቂቅ መነኮሳት የፈሉበት ጊዜ፣ ወዘተ... ወዘተ...
ሐ. ሁለቱ ሁኔታዎች ሲጠቃለሉ
እጅግ አሳሳቢ ችግሮች የተደቀኑባት ነገር ግን ይህንን ሁሉ ከቁብ ሳይጥፉ በጥቃቅን ጉዳዮች ተለያይተው፣ የክርስቶስን ሳይሆን የግላቸውን ብቻ እየተመለከቱ የሚናቆሩ አባቶች የሚያሽከረክሯት ቤተ ክርስቲያን እንዳለችን ያሳየናል፡፡ ታዲያ ምን ይሻላል?
(ይህ ጽሑፍ አስተያየት ሰጪዎችን ለመጋበዝ የተቀረጸ፣ የመወያያ ሐሳቦችን ያዘለ መነሻ ሐሳብ ነው፡፡)


1 comment:

Anonymous said...

ሰላም ለርሶ።
አስተያየት?
እኔና እኔን መሰል ተራ ምዕመናን ሁለት አማራጭ ያለን ይመስለኛል።
1. ዝም ብሎ መጪውን መጠበቅ።
2. በሁለቱም ወገን ያለው ምዕመን ከአባቶቹ የሚጠብቀው መለያየትን እንዳልሆነ አጠንክሮ ማሳሰብ። ገለልተኞቹ ብዙ የሚያሳስቡ አይመስለኝም። ይሄን አጋጣሚ የሃይማኖት ቅሰጣ ለማድረግ የሚጠብቁ ወገኖችን ግን መርሳት አያስፈልግም።

እንደሚሉት ቸር ያሰማን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)