January 22, 2007

በቀድሞው ፓትርያርክ የሚመራው የጳጳሳት ቡድን 9 ጳጳሳትን ሾመ፤

በቀድሞው ፓትርያርክ የሚመራው የጳጳሳት ቡድን 9 ጳጳሳትን ሾመ
የቤተ ክርስቲያን የኃዘን ቀን?

ይህ ጥር 13 ቀን 1999 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያን የኃዘን ቀን ቢባል የሚበዛበት አይመስለኝም፡፡ በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንደሚባለው በአባ ጳውሎስ ተደጋጋሚ ስሕተት ላይ የነአባ መልከጼዴቅ ከመስመር የወጣ አካሔድ ታክሎበት እነሆ ቤተ ክርስቲያናችንን ለዚህ መሳዩ መከፋፈል ሊያበቃት ችሏል፡፡ ለብዙ ጊዜ ተስፋ ተደርጎ የነበረው የቀድሞው ፓትርያርክ ከዚህ በፊት ባሳዩት ራስን መግዛት ይህንንም የነአባ መልከጼዴቅን ጉትጎታ ወደጎን ይሉታል የሚል ነበር፡፡ አልሆነም፡፡ እናም ትናንት እሑድ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳትን በአሜሪካ ሲሾሙ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ በተጨማሪ በካናዳም ለመሾም ተዘጋጅተዋል፡፡

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)