January 22, 2007

በቀድሞው ፓትርያርክ የሚመራው የጳጳሳት ቡድን 9 ጳጳሳትን ሾመ፤

በቀድሞው ፓትርያርክ የሚመራው የጳጳሳት ቡድን 9 ጳጳሳትን ሾመ
የቤተ ክርስቲያን የኃዘን ቀን?

ይህ ጥር 13 ቀን 1999 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያን የኃዘን ቀን ቢባል የሚበዛበት አይመስለኝም፡፡ በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንደሚባለው በአባ ጳውሎስ ተደጋጋሚ ስሕተት ላይ የነአባ መልከጼዴቅ ከመስመር የወጣ አካሔድ ታክሎበት እነሆ ቤተ ክርስቲያናችንን ለዚህ መሳዩ መከፋፈል ሊያበቃት ችሏል፡፡ ለብዙ ጊዜ ተስፋ ተደርጎ የነበረው የቀድሞው ፓትርያርክ ከዚህ በፊት ባሳዩት ራስን መግዛት ይህንንም የነአባ መልከጼዴቅን ጉትጎታ ወደጎን ይሉታል የሚል ነበር፡፡ አልሆነም፡፡ እናም ትናንት እሑድ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳትን በአሜሪካ ሲሾሙ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ በተጨማሪ በካናዳም ለመሾም ተዘጋጅተዋል፡፡

January 21, 2007

Clergy Oppose Ordination of Bishops

Ethiopian Orthodox Tewahido Church from 12 parishes in USA oppose ordination of bishops by the exiled patriarch Merqoryos and his "exiled synod". In a press release dispatched to the media, the clergy regarded the act as "Lutheran" rather than "Orthodox"፤ against the teachings of the Church.

ይህን መግለጫ ያወጡት የሚከተሉት አብያተ ክርስቲያናት ካህናት ናቸው፡፡

1. ርዕሰ አድባራት ቅ/ ማርያም ዋሽንግተን ዲሲ
2. አዲስ ዓለም ማርያም ታምፓ ፍሎሪዳ
3. ደ/ ብሥራት ቅ/ ገብርኤል አትላንታ ጆርጂያ
4. ርዕሰ አድባራት ደብረ ምሕረት ቅ/ ሚካኤል ዳላስ ቴክሳስ
5. መካነ ብርሃን ቅ/ሥላሴ ቫርለት ሰሜን ካሮላይና
6. ደብረ ሣሕል በዓታ ለማርያም ኒውዮርክ
7. ደብረ ገነት አማኑኤል ፊላዴልፍያ
8. ደ/ታቦር እግዚአብሔር አብ ራሊ ሰሜን ካሮላይና
9. ደ/ሰላም መድኃኔዓለም ሚኔሶታ
10. ቅ/ገብርኤል ሳንሆዜ ካሊፎርኒያ
11. መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ኒው ዮርክ
12. ደ/ሰላም መድኃኔዓለም ዴንቨር ኮሎራዶ

January 16, 2007

A Tale of Two Synods, Two Patriarchs

የሁለት ሲኖዶሶች እና ፓትርያርኮች ወግ
ነመራ ዋቀዮ ቶላ
በቅርቡ የሰማነውና በትልቅ ተስፋ የጠበቅነው በሁለቱ ፓትርያርኮች መካከል ሊጀመር የነበረው ውይይት ሳይወለድ መክኖ፣ ሳይተኮስ ደንብሾ፣ ሳይጀመር ተፈጽሞ፣ ይመጣል ተብሎ የተጠበቀው አስተዳደራዊ አንድነትም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ያልተገመተ ውጤት ባይሆንም የቤተ ክርስቲያኒቱ መጻዒ ሁኔታ ለሚያሳስባቸው ግን እንዲሆን የተፈለገ መደምደሚያ አልነበረም፡፡ ይሁን እንጂ የተፈራው ደርሷል፡፡ ውይይቱም ሳይካሔድ ቀርቷል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ ልዩነት እንዲቀጥል ለሚፈልጉ ወገኖችም ትልቅ እፎይታን ፈጥሯል፡፡
የዚህን ውይይት አለመሳካት በግሌ የምመለከተው በሚከተሉት ሁለት ሁኔታዎች መነጽር ነው፡፡


ሀ. ሁኔታ አንድ
1. ‹‹ነአምን በአሐዱ አምላክ›› የሚሉ አባቶችና ‹ሲኖዶሶች›፣
2. አንዲት ቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉ አባቶችና ‹ሲኖዶሶች› እንዲሁም ፓትርያርኮች፣
3. አንዲት ቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስስቲያንን የሚወክሉ ‹ሦስት› አስተዳደሮች፡፡ እነርሱም የአገር ቤቱ ‹የአባ ጳውሎስ› አስተዳደር፣ የዳያስጶራው የአባ ‹መርቆርዮስ› (የአባ መልከጼዴቅ አስተዳደር እንጂ የቀድሞው ፓትርያርክ አይደለም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ቢበዙም) አስተዳደር፣ እና ‹ገለልተኛው› የሁለቱም አይደለሁም ባዩ አስተዳደር፣ እንዲሁም በሁሉም በኩል ያሉ አያሌ አገልጋዮች ካህናትና ምዕመናን፡፡
ለ. ሁኔታ ሁለት
1. ቅን መሪ እረኛ-አባት ያጡ በጎች-ምእመናን፣
2. ነጻነት የሌላቸውና የተለያዩ ፍላጎቶች ባሏቸው ወገኖች የሚዘወሩ (እነርሱም በአገር ውስጥ ያለው በመንግሥት፣ በዳያስጶራ ያለው አብዛኛው ደግሞ በ‹ተቃዋሚዎች›) ሦስት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደሮች ፡፡
3. የአክራሪ እስላሞች ሰይፍ ‹ከዛሬ ነገ› እያለ ተስሎ የሚጠብቀው ክርስቲያንና ቤተ ክርስቲያን፣
4. የፕሮቴስታንቶች ቅሰጣ ያስበረገገው ምዕመን፣
5. ጠባቂና ረዳት ያጡ ገዳማትና አድባራት፣ አበው ሊቃውንትና ቅርሦች፣
6. ጵጵስናን ብቻ ተስፋ የሚያደርጉ ደቂቅ መነኮሳት የፈሉበት ጊዜ፣ ወዘተ... ወዘተ...
ሐ. ሁለቱ ሁኔታዎች ሲጠቃለሉ
እጅግ አሳሳቢ ችግሮች የተደቀኑባት ነገር ግን ይህንን ሁሉ ከቁብ ሳይጥፉ በጥቃቅን ጉዳዮች ተለያይተው፣ የክርስቶስን ሳይሆን የግላቸውን ብቻ እየተመለከቱ የሚናቆሩ አባቶች የሚያሽከረክሯት ቤተ ክርስቲያን እንዳለችን ያሳየናል፡፡ ታዲያ ምን ይሻላል?
(ይህ ጽሑፍ አስተያየት ሰጪዎችን ለመጋበዝ የተቀረጸ፣ የመወያያ ሐሳቦችን ያዘለ መነሻ ሐሳብ ነው፡፡)


January 14, 2007

Two Synod Dialogue Failed

The much awaited dialogue between the two Ethiopian Orthodox Church Synods failed. According to Deje-Selam sources, the issue could not go farther due to bishop Melketsedeq's stubborn approach. It is not clear what patriarch Merqoryos says.

January 12, 2007

Bishop Gabriel to Take Back Holy Synod Position Again

Deje-Selam learned bishop Gabriel agreed to take his Synod position back after an intense dialogue with delegates from Addis Ababa.

January 9, 2007

Holy Synod Send Messengers, Talks with the Exiled Bishops Expected

The Ethiopian Synod send a two bishops delegation to start dialog about Church Unity with patriarch Merqoreyos and bishops around him. Arch Bishops Zekariyas and Gorgoreyos reached USA a week ago.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)