December 12, 2006

ኢትዮጵያውያን በሰላምና በአንድነት ተረዳድቶ የመኖር ባህላቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያውያን በሰላምና በአንድነት ተረዳድቶ የመኖር ባህላቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ ታህሣስ 2/1999/ ኢትዮጵያውያን ከቀደምት አባቶቻቸውና እናቶቻቸው የወረሱትን ሰላም፣ ተረዳድቶ በአንድነት የመኖር ባህላቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አስገነዘቡ።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ባካሄዱት የግማሽ ቀን የሰላም ጉባዔ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች ከየሃይማኖታቸው ትውፊት በቀር ልዩነት የሌላቸው በመሆኑ አሁንም አብሮና ተባብሮ ለመኖር ይበልጥ ሊተጉ ይገባል። እግዚአብሄር የሰላምና የፍቅር አምላክ መሆኑን ሁሉም የሃይማኖት ቅዱሳት መጻሕፍት የሚያስተምሩ መሆኑን ጠቀመው፤ ሰላምን፣ ፍቅርንና አንድነትን በሰዎች መካከል ማስፈን፣ ሰዎችን ማቀራረብና አንድ ማድረግ በአጠቃላይም እግዚአብሔር የሚወደውን ሥራ ሁሉ መሥራት የእምነት ግዴታ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም የሕገወጦች እኩይ ተግባ በመካከላቸው ቅራኔንና ጥላቻን የሚያስከትል ሁኔታ እንዳይፈጥር ሁሉም ወገኖች በንቃትና በጥንቃቄ አንድነትንና ሰላምን አጽንተው መፈለግ እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል። ባለንበት ዘመን በዓለም ዙሪያ የሚመላለሱ ሕገ ወጦች በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የእስልምናን እምነት ሽፋን በማድረግ እኩይ ዓላማቸውን ለማራመድ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አሳሳቢ ሆኖ መገኘቱን ገልጸዋል። በሀገር ወዳድ ሰላም ፈላጊዎች የኢትዮጵያውያን ወገኖች ኅብረት ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ጎልቶና ዳብሮ እንደኖረ ሁሉ አሁንም ሕገ ወጦችን በመከላከሉ ረገድ የሁሉንም የተባበረ ጥረት እንደሚጠይቅ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዳክስ፣ የእስልምና፣ የካቶሊካዊትና የወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስትያን የሃይማኖት አባቶች ሰላምን አስመልክቶ ባወጡት የአቋም መግለጫ፤ ሰላም ለሁሉም መሠረት መሆኑን ሁሉም ወገን የፈጣሪን ቃል ከሰማና ትእዛዝ ከተቀበለ የሰላም ዋስትና የተረጋገጠ እንደሚሆን ገልጸዋል። ሰላም ለሰው ልጅ ከማናቸውም መሠረታዊ ፍላጎቶች በላይ ሊሟላ የሚገባው ተቀዳሚ ጉዳይ መሆኑንም አመልክተዋል። የአገር እድገት፣ ብልጽግናንና ልማትን ማምጣት የሚቻለው የተሟላ ሰላም በአገር በወገን መካከል መኖር ሲችል ብቻ እንደሆነም የሃይማኖት አባቶቹ በአቋም መግለጫቸው ገልጸዋል። ለሰዎች አለመግባባት መንስዔው የተለያዩ ምክንያቶች ቢሆኑም የመማር ማስተማርና የመረዳት ባጠቃላይም የእውቀት ከፍተኛው መለኪያ ሰላም ማምጣት በመሆኑ ሁሉም ኅብረተሰብ የሰላምን ጥያቄ ተቀዳሚ አጀንዳ ሊያደርግ እንደሚገባ አስታውቀዋል። ሰላም ማለት ፍትህን ማምጣትና ተባብሮና ተረዳድቶ መኖር፣ በታማኝነትና በቅንነት መሥራት ስለሆነ ማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል ሰላምን ለማምጣት ከሚጀያደርገው ጥረት አኳያ ለሰላምና እንቅፋት ሊሆኑ ከሚችሉ ሁኔታዎች ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ መጠንቀቅ እንደሚኖርነትም አስገንዝበዋል። ባለፉት ወራት በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ ኢትዮጵያ እኩይ አላማ ባላቸው ግለሰቦች ድርጊት የሰው ህይወት መጥፋቱንና የንብረት ውድመትና ዝርፊያ ማካሄዱን አመልክተዋል። ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆኑ ህገወጦች በፌደራልና በክልል መንግስታት ከትትል ህግ ፊት መቅረባቸወውን አመልከተው ተቻችሎና ተከባብሮ የኖረውን ህብረተሰብ አንድነት ለማናጋት የተቃጣው ሙከራ እጅግ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። የሀይማኖት አባቶች በተለያዩ ወቅት በአገር ላይ በሚከሰቱ ችግሮች ዙሪያ ላ/የ ሰላምን ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበርና አሁንም ይህንን ጥረታቸውን ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀይማኖት አባቶች በአቀቋም መግላጫቸው አስታውቀዋል። አዲስ ዘመንspan tags

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)