(ተረፈ ወርቁ):- "... እንደው እነዚህ በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች እንደምንም
ብለው ተጠናክረው በአገራችን በኢትዮጵያ በእነርሱ በሚመራው በአሜሪካው "ሲኖዶስ" ሥር ያለ/የሚመራ አንድ እንኳን
ቤተ ክርስቲያን መመሥረት ቢችሉ በየቦታው ተበታትኖ ያለውን የተሃድሶ እንቅስቃሴ አንድ ማድረግ መምራት ይቻል ነበር እኮ ...።"
ይህ ቁጭት፣ ምሬት አዘል ቃል በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን ቤ/ን እናድሳለን ብለው
ከተነሡ ሰዎች መካከል ማህበር አቋቁሞና ከአንዳንድ ስለ ሃይማኖታቸው በቂ የሆነ መሠረት ከሌላቸውና የእውነት ዕውቀትን በፍቅር ካልተቀበሉና
እንደ "ዘመነ መሳፍንቱ" - የባላባቶች ዘመን "አወዳሽና አንጋሽ" ፈላጊ በሆኑ ባለ ጠጋዎች፣ ወይዛዝርት፣
ነጋዴዎች ምጽዋትና እንዲሁም ከውጭ አገር በሚላክለት ዶላር (በተለይ ከዱባይና ከአሜሪካ) በዐሥር ሺዎች የሚገመት ዘመናዊ ቤት/አዳራሽ
ተከራይቶ የተሐድሶን እንቅስቃሴ ለማስፋፋት ላለፉት 20 ዓመታት እየደከመ ያለ ሰው የተናገረው ምሬት ያዘለ ቃል ነው። ለነገሩ ይህ
ማህበር በነጋ ጠባ ራሳቸውን በሾሙ በጎበዝ አለቆች የሥልጣን ይገባኛልና በጥቅም ግጭት ሲፈርስ ሲሠራ የኖረ፣ እንዳሰቡትና እንዳለሙት
እንኳን የኢትዮጵያን ቤ/ን ሊወርሱ ቀርቶ የሕልም ዳቦቸውን እየገመጡ በቀቢፀ ተስፋ ተውጠው ነው ያሉት።